የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች የከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽኖች እና የፕላንቶች መለዋወጫ ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Addis Ababa City Roads Authority (የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አስከመባ/ግብዓት/ቡ-2/001-2/2017
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪዎች የከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የኮንስትራክሽን ማሽኖች እና የፕላንቶች መለዋወጫ ዕቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተቁ |
የሚገዛው ዕቃ ዓይነት |
የጨረታ መ/ቁጥር |
ጨረታ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|
ሎት 1 |
የቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች |
አአከመባ/ግብዓት/ቡ-2/001-2/2017 |
60 ቀን |
መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት |
መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት |
100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) |
|
ሎት 2 |
የከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች |
150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) |
||||
|
ሎት 3 |
የኮንስትራክሽን ማሽኖች መለዋወጫ ዕቃዎች |
250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) |
||||
|
ሎት 4 |
የተለያዩ የፕላንቶች መለዋወጫ ዕቃዎች |
10,000.00 (አስር ሺህ ብር) |
ስለዚህ
-
ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWW.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ መቅረብ የሚገባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ certified payment order (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional Bank Guarantee/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተበሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 011-3-72-28-25/011-3-71-41-03
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
