መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባህር ዳር ቅ/ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባህር ዳር ቅ/ፅ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ - ESS-001-BAO-CW-2017
መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነድ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ)
|
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የእድሳት እና የግንባታ እንዲሁም ተያያዥ ስራዎች |
100.00
|
50,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆናቸውን የሚያሳይ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ ታክስ ክሊራን ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባህር ዳር ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 50,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የግንባታ ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል::
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8:30 ሰዓት በአዲሱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ :- 0583209095/0918027577/0911092323
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባህር ዳር ቅ/ፅ/ቤት
