የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ ቀይት ቀበሌ አመር አገር ልዩ ስሙ ቦለድ አካባቢ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሸን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን ለ400 ሰዓት በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለምርት ግብዓት የሚሆን ባህርዛፍ ግንድ ቀይት ቀበሌ አመር አገር ልዩ ስሙ ቦለድ አካባቢ እና ቀይት ቀበሌ ልዩ ስሙ አይሶፌ አካባቢ ደን ሳይት ስለሚጭን ለሚጭኑት ገልባጭ መኪኖች መተላለፊያ የሚያገለግል በጫካው ውስጥ ለውስጥ ጊዜያዊ መንገድ በኤክስካቫተር ማሸን የጠረጋ ስራ ማሰራት እንዲችል በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር ውል በመግባት ማሽኑን ለ400 ሰዓት በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
- በዘርፉ የተሰማራና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው፣
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 – 3 የተጠቀሱትና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው::
- አሸናፊው ድርጅት ማሽኑን በራሱ ወጪ /የሎቤድ ኪራይ ራሱ ችሎ/ ስራው የሚሰራበት ጫካ ድረስ የማድረስና ስራውን ሲጨርስ የመመለስ ግዴታ አለበት፣ እንዲሁም የራሱ ኦፕሬተር ሊኖረው ይገባል፤ የኦፕሬተር ሰርቪስ ተጫራቹ ማቅረብ አለበት፡፡
- የአንዱ ሳይት ሥራ ሲጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ሳይት ማሽኑን የማዘዋወር ኃላፊነት የአከራዩ ድርጅት ኃላፊነት ነው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች በስራ ቦታ ላይ ከነዳጅ ወጪ በስተቀር የኤክስካቫተሩን የዘይት ቅባት፣ ግሪስ፣ ሰርቪስ፣ ቀላልና ከባድ ጥገናዎች፣ የጎማ ጥገናና ግዢ፣ የሹፌር ደመወዝ እና አበል እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
- ማሽኑ በስራ ላይ እያለ ቢበላሽ አሸናፊው ተጫራች በራሱ ወጪ የተበላሸውን የማስተካከል ስራ የሚሰራ ሲሆን በቀላሉ ማስተካከል የማይችል ከሆነ በራሱ ወጪ አንስቶ በምትኩ ሌላ ማሽን የማስገባት ግዴታ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፤ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ላይ ወይም እሁድ ከዋለ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከካምፓኒው ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910368437 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
