Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline15 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-15 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሀዋሳ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለሚያሠራው ነባር የጎርፍ መውረጃ ቦይ ጥገና ሥራ ሎት 01 እና የጎርፍ መውረጃ ቦይ አፍርሶ መስራትና የኮብልስቶን ጥገና ሥራ ሎት 02 በመስኩ የተሠማሩ ልምድ ያላቸውን ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀዋሳ ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ለሚያሠራው ነባር የጎርፍ መውረጃ ቦይ ጥገና ሥራ ሎት 01 እና የጎርፍ መውረጃ ቦይ አፍርሶ መስራትና የኮብልስቶን ጥገና ሥራ ሎት 02 በመስኩ የተሠማሩ ልምድ ያላቸውን ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድረጃቸው GC-9 ኮንስትራክሽን ዘርፍ የሆኑ ማህበራት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በሥራ መስኩ ሀጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ ሲፒኦ (ባንክ ጋራንቲ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ22ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡
  6. ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚገባበትና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
  7. በሥራ ተቋራጭ የቀረበው ዋጋ ከመሀንዲስ ግምት ከ15% በላይ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ውድቅ ይሆናል፡፡
  8. በፋይናንሻል አከፋፈት የተነበበው ዋጋ ከአርቲሜቲከ በኋላ ካለው ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት ከ2% በላይ/በታች ከሆነ የቀረበው ዋጋ ውድቅ ይሆናል፡፡
  9. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበው የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች (ከአሥራ አምስት ፐርሰንት) 15% በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis Sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር-046-2-12-13-34

 

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ልማት መምሪያ

 

Save Tender