የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ በሥሩ ለሚገኙ ጤና አጠባበቅ ተቋማት አገልግሎት የሚውል IoKVA (AC) ትናንሽ ጄኔሬተሮች አልትራሳውንድ እና ላውንደሪ ማሽን ግዥ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ በሥሩ ለሚገኙ ጤና አጠባበቅ ተቋማት አገልግሎት የሚውል IoKVA (AC) ትናንሽ ጄኔሬተሮች አልትራሳውንድ እና ላውንደሪ ማሽን ግዥ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
- ትናንሽ ጄኔሬተሮች 10KVA (AC)-ሎት 01/2017
- አልትራሳውንድ - ሎት 02/2017
- ላውንደሪ ማሽን - ሎት 03/2017
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ከግዥ ንብ/አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በሰም ለየብቻቸው በታሸጉ ኤንቨሎፖች አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል እና ለማሽነሪዎች አስፈላጊ የሆኑት በስፔክዮ የተቀመጡ ቴክኒካል ሰነዶችን አሟልተውና አያይዘው በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 3:30 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መም/ያ
