Tender Detail

Tender Details

  • Company ጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address , Phone: 0113320641
  • Website
  • Deadline23 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-23 00:00:00
  • Categories Building Construction

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የG+2 የቢሮ ግንባታ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ግልፅ የጨረታ ቁጥር፡- ጉ/ከ/አስ/1189/07/2017

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው የG+2 የቢሮ ግንባታ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ፦

  1. ደረጃ BCS/GC5 እና ከዚህ በላይ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ ቲን ነምበር ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ከቀን 15/7/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15/08/2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 30 ቀናት እስከ 30ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ደረስ የማይመሰስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡።

ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊከ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት/ የጨረታ ማስከበሪያ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከኦሪጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ፤

ለ/ ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ አሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ/ ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ 30ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

  1. የጨረታ ማስከበሪያ ለ9ዐ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት ይኖርበታል፡፡
  2. ጨረታው በቀን 15/08/2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ሰዓት ላይ በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በይፋ ይከፈታል፡፡ ተቋራጮች (ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  3. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሳሰቢያ፡-

1ኛ/ በአፈፃፀማቸው ምክንያት 3ኛ ዙር ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም፡፡

2ኛ/ የህንፃው ግንባታ የሚከናወንበት ቦታ ተቋራጮች ከጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ቦታውን መጎብኘትና መጎብኘታቸው የሚያስረዳ መረጃ ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3ኛ/ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን በሚከታተላቸው ፕሮጀክቶች ከአንድ በላይ ፕሮጀክት ያለው ተቋራጭ መወዳደር አይችልም፡፡

4ኛ/ በጨረታው ሂደት ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ ግዢ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

5ኛ/ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-3-32-05-91 ይደውሉ፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጉራጌ ዞን የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender