በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ሥራና ክህሎት ኢንተፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮና ለሰልጣኞች መቀመጫ የሚያገለግሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ሥራና ክህሎት ኢንተፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮና ለሰልጣኞች መቀመጫ የሚያገለግሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት:-
- በዘርፉ የታሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ በግብር ከፋይነት የተመዘገበ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የ2017 ዓ.ም የግብር ግዴታውን የተወጣ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉበት የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝና የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብቻ ሲዳማ ባንክ በኮሌጁ ስም በተከፈተው የሂሳብ ቁጥ 3428302000039 በመክፈልና ደረሰኝ በማቀረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቱን ጀምር እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት በይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልጽ በመሙላት በህተምና በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚሞላው ዋጋ (15%) ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 30% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
- ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል የማይዋዋል ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን የፈርኒቸሩን ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ መጓጓዣ እስከ ኮሌጁ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛውም ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያውኑ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ሰዓት የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ወይም 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 046-225-15-62 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
