በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለወረዳ የትምህር ጽ/ቤት ፣ ለህዝብ ምክር ቤት የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ጨረታ እና የኢንተርፕራይዞች ማምረቻና መሸጫ ሼድ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለወረዳ የትምህር ጽ/ቤት ፣ ለህዝብ ምክር ቤት የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ጨረታ እና የኢንተርፕራይዞች ማምረቻና መሸጫ ሼድ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ የትምህር ጽ/ቤት የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ጨረታ
- ሎት ሁለት የህዝብ ምክር ቤት የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ጨረታ
- ሎት ሶስት የኢንተርፕራይዞች አንድ ማዕከል ጽ/ቤት ግንባታ ጨረታ
በዚህም መሠረት ከታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚታሟሉ ተጫራቾች እንዲትወዳደሩ እንጋብዛለን።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ያላት፣
- የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው ያላት፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/የከፈለች፣
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ያላት፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች፣
- የሙያ ፈቃድ GC ወይም BC ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የግንባታ ቦታ የጎበኙበት ደብዳቤ ከአሰሪው መ/ቤት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- ደረጃ ሰባት እና በላይ (አንድ እስከ ሰባት)፣
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችል/የምትችል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-10 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት አንድ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ21ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በ21ኛው ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሎት ሁለት ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ21ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በ21ኛው ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሎት ሶስት ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ21ኛው ቀን 9፡30 ታሽጎ በ21ኛው ቀን 10፡00 ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
ማሳሰቢያ:-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ፡፡
በጎፋ ዞን የመሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
