በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለሚገኙ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ተቋማት አገልግሎት የሚውል የኢንሹራንስ አገልግሎት እና የገንዘብ መመሪያ ቢሮ ጥገና ግንባታ ስራ በተጨማሪም ሸራተን አዲስ ወንበር አቅርቦት ግዥን በሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሸራተን ወንበር አቅርቦት፣ የቢሮ ግንባታ ጥገና እና ኢንሹራንስ አገልግሎት ግዥ ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለሚገኙ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ተቋማት አገልግሎት የሚውል የኢንሹራንስ አገልግሎት እና የገንዘብ መመሪያ ቢሮ ጥገና ግንባታ ስራ በተጨማሪም ሸራተን አዲስ ወንበር አቅርቦት ግዥን በሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ከሚወዳደሩት ስራ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆና የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ለቢሮ ጥገና ግንባታ ስራው ደረጃ 10 እና ከዛ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer Identification Number) ያላቸው::
- በግዥ አፈጻጸም መመሪያው የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ውጭ የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት /ምድብ/ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ/ በመክፈል የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት /ምድብ/ ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርዓት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስራ አምስተኛ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናውን በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጥዋቱ 3፡05 ይከፈታል፣ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል።
- መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/ኢ/ት/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በአካል መገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334401230/0249/0062 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
