የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለመንገድ ግንባታ ጥገና ፕሮጀክት ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች ማሠራት ይፈልጋል።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
በድጋሚ የወጣ ግልጹ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/025/2017
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለመንገድ ግንባታ ጥገና ፕሮጀክት ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልሉ ውስጥ መንገዱ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት ኪ./ሜ |
|
ሎት-5 |
ሀገር ስላም ጋታማ |
ሁላ |
8.3 |
|
|
ቃዋዶ አበራ ሁላ |
ሁላ ዳራ ኦትልቾ |
9 |
|
|
ሽልቾ አበራ |
ዳራ ሁቲልቻ |
13.5 |
|
ሎት-7 |
ማጆ ዳኤላ |
አሮሬሳ/ ዳኤላ |
10 |
|
|
ማጆ ግርጃ |
አሮሬሳ / ግርጃ |
9 |
|
ሎት-1 |
ጊዳቦ አስፋልት አዶቴ ቃቻ |
አላታ ወንዶ |
2 |
|
|
ሀሮ ከሞልቻ አበራ |
ዳራ ኦትልቾ |
3.5 |
በዚህ መሰረት ፤-
- የኮንስትራክሽን መሣሪየዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሆን አለባቸው ፡፡
- ገልባጭ መኪና እስከነሎደር የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ 2010 እና ከዚያ በላይ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም=14m3 መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም E-trade ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ገልባጭ መኪኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አዲስ ስራ ፍቃድ እና ስራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፡፡
- ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቂያ የደረሰው ስራውን ያላጠናቀቀና ውሉ የተቋረጠ የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነድን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችልም ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በድጋሚ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል ።
- በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደርዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠየቀው የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
