Tender Detail

Tender Details

  • Company የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አምቦ ከተማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112609448
  • Website
  • Deadline24 Mar 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-03-24 00:00:00
  • Categories

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ጋራጋንቲ የሚያመርት ዶዘር አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መከራየት ስለሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ለ3ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 04/2017

 

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ጋራጋንቲ የሚያመርት ዶዘር አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መከራየት ስለሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፦

  1. ከተጠቀሰው ሥራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው፣ የ2017 የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው ፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ (supplier list) ሆኖ ከሚመለከተው አካል ማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 2% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፡፡
  2. ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነጻ የሆና እና የሀገሪቱን እና የክልሉን ሕግ የሚያከብር፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራቶች በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ሲፒኦ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር የገንዘብ መጠን ህጋዊ እና ዕውቅና ካለው ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. የጨረታ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት።
  5.  በጨረታ ሠነዱ ላይ ሥልጣን ባለው አካል /የድርጅቱ ባለቤት/ ሥም ፣ ፊርማ ፣ የድርጅቱን ማህተም ፣ የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መገለጽ አለበት፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታውን ኦርጅናል ከኮፒው ጋር በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7.  የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ15/7/2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት የጨረታውን ሣጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባለመገኘታቸው ምከንያት ጨረታውን ከመከፈት አይስቀርም፡፡ ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9.  የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ሾርት ኮድ (short code) 518220 እና አብሬተር አይድ (Operator ID) 176959 ላይ በመክፈል በማስገባት የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን የሚሰጣቸውን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በደብዳቤ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ10ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር ሕጋዊ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
  11. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞክር ከጨረታው ዉጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊት በማንኛውም የመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  12. በሳይት ቆይታው የዶዘሩን ጥበቃ የኦፕሬተር ዉሎ አበል፣ ነዳጅ፣ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን በአሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0112609448/0112364462

 

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender