Tender Detail

Tender Details

  • Company AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4403766
  • Website
  • Deadline02 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-02 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Office And Home Furniture , Materials , Vehicle Battery , Cloth And Shoes

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

AA Kaliti Customs Office (አ.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


 

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 35/2017

 

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም በግልጽ ዕቃ ጨረታ ላይ የሚሣተፉ ተጫራቾች ሰነዱን ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ባመቻቸው የበየነ መረብ (Online) የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የሚያገኙ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም፣

  1. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ባመቻቸው የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሰነዶቹን በማያያዝ በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  3. ተጫራቾች የዕቃዎችን የግልዕ ጨረታውን ሠነድ ከሐሙስ መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የግልፅ ጨረታውን ሰነድ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ድረ-ገፅ auction.et ላይ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ያገኙታል፡፡
  4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

የእቃ ግልጽ

እስከ 23/07/2017 ዓ.ም

24/07/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- ኢ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ እንዲሁም በበይነ መረብ (Online) የሚጫረቱ ተጫራቶች በድረ ገፁ መከታተል ይችላሉ።
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ወይም በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ድረ-ገፅ auction.et ላይ ከተጫረቱ ደግሞ ከጨረታው በኋላ ይመለስላቸዋል።
  3. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት CPO እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ፦ 011-470-85-03 እንዲሁም የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/ 011-666-88-28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፡- በዕቃ ግልጽ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከቀረቡት ሁለት የመጫረቻ አማራጮች መካከል በተመቻቸው በአንዱ ብቻ መጫረት የሚችሉ ሲሆን በአንድ ተጫራች ስም በሁለቱም አማራጮች መጫረት ከጨረታው የሚያሰረዝ ይሆናል፡፡ በኦንላይን መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማኅበር ድረ-ገፅ መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በኦንላይን የተወዳደሩ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በአካል መምጣት ሳያስፈልግ በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገደ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቦሌ አትላስ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ. 301

 

በጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender