Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-1-13-08-59
  • Website
  • Deadline22 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-22 00:00:00
  • Categories Water Construction Machinery And Equipment , Construction Materials And Raw Materials

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳባት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት /DRDIP-ll/ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አራት ቀበሌዎች ማለትም ቀበሌ-03 ቀበሌ-04 ፣ ጭላ ቀበሌ እና በንከር ቀበሌ የመንገድ ግንባታ ሥራ አስፈላጊውን ጥሬ እቃና መሳሪያ አቅርቦ ለሚሰራ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2017 ዓ.ም

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳባት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት /DRDIP-ll/ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በከተማው ውስጥ ለሚገኙ አራት ቀበሌዎች ማለትም ቀበሌ-03 ቀበሌ-04 ፣ ጭላ ቀበሌ እና በንከር ቀበሌ የመንገድ ግንባታ ሥራ አስፈላጊውን ጥሬ እቃና መሳሪያ አቅርቦ ለሚሰራ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፦

  1. ደረጃቸው RC-4/GC-4 እና ከዛ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፣ የተ.እ.ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት ቁጥር (TIN No) እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል እና የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ስለስራው ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ. ቁጥር 08 መውሰድ ይችላሉ።
  3. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ30 (ስላሳ) ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ31ኛው (ሰላሳ አንደኛው) ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ዶክመት 1 (አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ ለየብቻ ታሽገ በአንድ ፖስታ በተመሳሳይ ፋይናሽያል ሰነድ 1 (አንድ) ኦሪጅናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ፖስታ ለብቻ በማሸግ የድርጅቱን ክብ ማህተም በማሳረፍ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Security) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከታወቀ ባንክ ብቻ ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  6. ተጫራቾች የተጠቀሙትን የኳሪ ሳይት በራሳቸው ወጪ መልሰው መድፈን አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የውድድር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም መኖር ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከታወቀ ባንክ ብቻ ማስያዝ አለበት፡፡
  10. አሰሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-1-13-08-59 መደወል ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዳባት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender