Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል
  • Address ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033 312 49 56
  • Website
  • Deadline06 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-06 00:00:00
  • Categories Medical Equipment And Supplies

የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለፊዚዮቴራፒና ለዊልቸር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለፊዚዮቴራፒና ለዊልቸር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፦

    1. የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የግብር መክፈያ ቁጥር /TIN/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፡፡
    2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰትን የሚያሟላ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይችላሉ፡፡
    3. የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር ሲ.ፒ.ኦ /ጥሬ ገንዘብ/ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
    4. የጨረታ ውድድሩ የሚደረገው በሎት ነው፡፡
    5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው ይከፈታል፡፡
    6. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሁሉም ተጫራቾች በአካል ባይገኙም በዕለቱ የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ ከታየ በኋላ ተገቢው የጨረታ ማስከበሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ ተጫራቹ በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል፡፡
    7. የጨረታ አሸናፊው በተሰጠው የጨረታ ሰነድ /Specification/ መሰረት እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት አጎጉዞ በሚመለከታቸው ባለሙያ እየተረጋገጠ ለማእከሉ ን/ክፍል በሞ/19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል ፡፡
    8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 033 312 49 56፣ 033 311 70 48 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
    9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል

Save Tender