የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የዋና መ/ቤቱን ህንጻ ወለሎች ምንጣፍ ማስነጠፍ ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 29/2017
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የዋና መ/ቤቱን ህንጻ ወለሎች ምንጣፍ ማስነጠፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉ ምንጣፎችን የማቅረብ፤ የማንጠፍ አገልግሎትን ጨምሮ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶችን ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች አግባብነት ያለው የዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት (VAT)፤ የግብር ክፍያ መለያ የምስክር ወረቀት (TIN)፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከግብርና ታክስ ሰብሳቢ መ/ቤቶች የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ/የመጫረቻ ሰነዶች በታሸጉ ኢንቨሎፖች በአንድ ኦሪጂናልና በአንድ ኮፒ እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 602 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የሚለጠፍ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር :- 011-551-32 88
ፖ.ሳ.ቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
