Tender Detail

Tender Details

  • Company ቢኤም ኢትዮጵያ የልብስ ስፌት እና ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ
  • Address ኢትዯጵያ, Phone: +251-988347038
  • Website
  • Deadline02 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-04 00:00:00
  • Categories Spare Parts , Vehicle

ቢኤም ኢትዮጵያ ልብስ ስፊት እና ጨርቃጨርቅ አ.ማ በስሩ ያሉ የመለዋወጫ እቃዎች እና ለረጅም ግዜ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ቢኤም ኢትዮጵያ የልብስ ስፌት እና ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ቢኤም ኢትዮጵያ ልብስ ስፊት እና ጨርቃጨርቅ አ.ማ በስሩ ያሉ የመለዋወጫ እቃዎች እና ለረጅም ግዜ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የመለዋወጫ እቃዎች እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ፣ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ፣ በቀድሞው የአደይ አበባ ድር እና ማግ ፋብሪካ (ቁጥር 2) የአሁኑ ቢኤም ጨርቃጨርቅ አ.ማ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከቀን 15/07/2017 ዓ.ም እስከ 22/07/2017 ዓ.ም ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት በአካል ቀርቦ በማየት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ለቀረቡት የመለዋወጫ እቃዎች እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች መነሻ ዋጋ ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ከጨረታው ቀን በፊት የባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከቀን 23/05/2017 ዓ.ም እስከ 24/05/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ከቀኑ 7:30 ሰዓት ድረስ በቢኤም ኢትዮጵያ ልብስ ሰፊት እና ጨርቃጨርቅ አ.ማ ቅጥር ግቢ በውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅፅ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ ተብሎ ተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን የሰነድ ማቅረቢያ ከገዙ በኋላ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ለድርጅት ሲሆን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር እና የባንክ ሲፒኦ ለግለሰብ ሲሆን የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በቀን 26/07/2017 ዓ.ም በድርጅቱ ውስጥ ባለው አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ባሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15 በመቶ በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
  7. ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ በመክፈል ንብረቶቹን ካልተረከቡ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታውን አሸንፈውና ከፍያውን ፈፅመው ንብረቱን በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ካላወጡ ንብረቱ ለተቀመጠበት በየቀኑ ብር 2,000 (ሁለት ሺ ብር) ከፍለው ይወስዳሉ፡፡
  9. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-988347038 እና 251-913034733 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

ቢኤም ኢትዮጵያ ልብስ ስፌት እና ጨርቃ ጨርቅ አ.ማ

Save Tender