ቦስተን ፓርትነርስ ሃላ/የተ/የግል ማህበር/ኩሪፍቱ ሪዞርት/ ለሪዞርቶቹ ለላውደሪ፣ ለሃውስኪፒንግ እንዲሁም ለማብሰያ እቃዎች/ኪችን ጽዳት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ብራንድ ኬሚካሎችን፣ የጽሕፈት መሳሪያዎችን እንዲሁም ለድርጅቱ መኪናዎች ጥገና እና ሰርቪስ ሰጪ ጋራጆችን በጨረታ አወዳድሮ በቀጣይነት ለሪዞርቶቹ የሚያቀርብ አቅራቢ እና አገልግሎት ሰጪ /ጋራጅ/ አወዳድሮ በቀጣይነት አብሮ መስራት ይፈልጋል፡፡
ቦስተን ፓርትነርስ ሃላ/የተ/የግል/ማህበር/ኩሪፍቱ ሪዞርትስ/
የጨረታ ማስታወቂያ

- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ከቦስተን ፓርትነርስ ሃላ/የተ/የግል ማህበር አድራሻ ቦሌ መንገድ ቦስተን ፓርትነርስ ህንጻ አራተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከሰኞ መጋቢት 22 እስከ አርብ መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ለጨረታው የሚቀርብ ማንኛውም ተወዳዳሪ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ /TIN Certificate/ እንዲሁም የቫት ምስክር ወረቀት /VAT Certificate/ ያለው መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለአንድ አመት በቋሚነት የሚያገለግል ይሆናል።
- አገልግሎት ሰጪ /የጋራጅ/ ተጫራቾች ሰነድ መግዛት ሳይኖርባቸው ለሰርቪስ የሚያስከፍሉትን ዋጋ እንዲሁም እየሰሩ ካሉባቸው ድርጅቶች የምስክር ወረቀት ጋር በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አቅራቢዎች ምርቶቹን ቦሌ መንገድ በሚገኘው ቦስተን ፓርትነርስ ህንጻ መረከቢያ ቦታ ይሆናል፡፡
- የጽህፈት መሳሪያ አሸናፊዎች ሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው የእቃ ብራንድ ውጪ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ በኋላ ተመላሽ የሚሆን ብር ሁለት ሺህ (2,000.00) በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። CPO ያላስያዘ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- የኬሚካል ጨረታ አሸናፊ ድርጅት የኬሚካል አጠቃቀም እና ተዛማጅ ስልጠናዎችን የመስጠት እንዲሁም ምርቱን ለመጠቀም የሚረዱ እቃዎችን የማቅረብ ፤ የመግጠም ሃላፊነት አለበት።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከሰኞ መጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 03 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 18 43 64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ቦስተን ፓርትነርስ ሃላ/የተ/የግል/ማህበር/ኩሪፍቱ ሪዞርትስ/