የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ የሚውሉ የተለያዩ የፖሊስ አልባሳት እና ተያያዥ ግዥን በተመለከተ የማማከር አገልግሎት ግዥ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
ግ/ጨ/11/2017 የበጀት ዓመት
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ የሚውሉ የተለያዩ የፖሊስ አልባሳት እና ተያያዥ ግዥን በተመለከተ የማማከር አገልግሎት ግዥ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡-
የተለያዩ የፖሊስ አልባሳቶች እና ተያያዥ ግዥን በተመለከተ የማማከር አገልግሎት ግዥ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ህጋዊ የ2017 የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስይዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በየሎቱ ለየብቻ በማዘጋጀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ10 (አስር) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎችን በራሳቸው ወጪ የማጓጓዣ መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ ቫት እና ማንኛውንም ወጭን ጨምሮ መሙላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን የቀረበው ዋጋ ወጪን አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 23/07/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ23/07/2017 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አባበ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አካባቢ
ተጨማሪ መረጃ፡- 0913108990 ወይም 0996054778 መደወል ይችላሉ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
