በአብክመ በደ/ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ለወረኢሉ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለሚያስገነባቸው 1ኛ. የካቤ ከተማ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ባለ 4 ክፍል አንድ ብሎከ ግንባታ በአልማ በጀት 2ኛ. የሰኞ ገቢያ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ባለ 4 ክፍል አንድ ብሎከ ግንባታ እንዲሁም 3ኛ. የወረኢሉ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ፑል ሙሉ አጥር በመደበኛ ካፒታል በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በደ/ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽቤት ለወረኢሉ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ለሚያስገነባቸው 1ኛ. የካቤ ከተማ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ባለ 4 ክፍል አንድ ብሎከ ግንባታ በአልማ በጀት 2ኛ. የሰኞ ገቢያ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ባለ 4 ክፍል አንድ ብሎከ ግንባታ እንዲሁም 3ኛ. የወረኢሉ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ፑል ሙሉ አጥር በመደበኛ ካፒታል በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ የስራ ተቀራጮች
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው እና የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ከደረጃ G.C/B.c 7 እና በላይ የሙያ ፈቃድ ያላችሁና በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- የመልካም ስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ከታወቀ የመንግስት ወይም NGO ማቅረብ የሚችልና ላቀረበው የመልካም ስራ አፈጻጸም ጊዜያዊ/ ፋይናል ርክክብ የተደረገበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ለካቤ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለሰኞ ገበያ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለእያንዳንዳቸው በተናጠል 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለወረኢሉ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ፑል ሙሉ አጥር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላ ባዶ ቦታ ከተገኘ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል።
- የሚሰራውን የስራ ዝርዝር /bill of quantity/ እንዲሁም የግንባታውን ዲዛይን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰዓት በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት ላይ የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ በሁሉም ሰነዶች ላይ የመጫረቻ ሰነድ፣ ሌሎች ሰነዶች እንዲሁም የግንባታውን ፕላን ጨምሮ ኦርጂናል የድርጂቱን ማህተም በመጠቀም እና በመፈረም በጥንቃቄ በ2 ፖስታ በማሸግ በወረዳው ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ እንዲሁም ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተዘረዘሩትን ኦርጂናል ሰነዶችን ለማመሳከሪያነት በእጅ በመያዝ በጨረታ መክፈቻው ዕለት መገኘት አለባቸው ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በእለቱ ለሚፈጠር ችግር ተጫራቾች በተራ ቁጥር 9 ላይ በተቀመጠው አንቀጽ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ድረስ በአየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡
- የመጫረቻ ሰነድ ጸንቶ የመቆያ ጊዜው ይህ ጨረታ ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር ለ40 ቀናት ይሆናል ።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለተጨማሪ መረጃ ወረኢሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033 116 01 99/54 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
