በደቡብ ምዕራብ ኢት/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዘመን በተያዘ ካፒታል ፕሮጀክት በጀት በግቢው ውስጥ የአጥር ግንባታ ስራ የተጫራቾች ደረጃ /BC/GC -6/ስድስት/ እና ከዚያ በላይ በሆኑ ጠቅላላ ህንፃ ተቋራጭ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቦ/ፖ/ቴ/ኮ 003
በደቡብ ምዕራብ ኢት/ህ/ክ/መንግስት በካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዘመን በተያዘ ካፒታል ፕሮጀክት በጀት በግቢው ውስጥ የአጥር ግንባታ ስራ የተጫራቾች ደረጃ /BC/GC -6/ስድስት/ እና ከዚያ በላይ በሆኑ ጠቅላላ ህንፃ ተቋራጭ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፣
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ፤ የቫት እና የቲን ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000029122877 በሆነው ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለተከታታይ 21 /ሃያ አንድ /ቀናት በኮሌጁ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው መሰረት ዋጋውን በመሙላት ዋናውን ከ2 /ሁለት/ ኮፒ ጋር ለየብቻ ፖስታውን በኤንቬሎፕ በማሸግ 3ቱን በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ የድርጅቱን ማህተም፤ ፊርማ እና ስም በማኖር በ22ኛው ቀን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በወጣበት በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው መታሸጊና መክፈቻ ሰዓት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መከፈት ስነ ስርዓት እያስተጓጉልም፡፡
- ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ የብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO /Certified Payment order/ ብቻ በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም በማሰራት ከኦርጅናል ጨረታ ሠነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ቢድቦንድ እና ቼክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- ተጫራቾች ለውድድር ብቁ መሆናቸውን የሚገልጽ ከዚህ ቀደም ከሰሩበት አሰሪ መ/ቤት እና ከተቆጣጣሪ ቢሮ መልካም የስራ አፈፃፀም የድጋፍ ደብዳቤን ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የግንባታ የስራ ውለታ ያላቋረጡና በአሁኑ ሰዓት ምንም ስራ ያለመኖራቸውን ከከተማና ከዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ አሠሪው ኮሌጅ ድረስ በመገኘት ውል መግባት አለበት፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917916439/0979724757 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ካፋ ዞን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
