ቀበና ናዳ ገበያ ማእከል አክሲዮን ማህበር በሰሚት 72 የሚገኘውን 2B G+7 ቅይጥ ህንጻ የማጠቃለያ (ፊኒሺንግ) ሥራ ለማሰራት የህንጻ ወይም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ለማጫረት ይፈልጋል (labor Contract)::
ቀበና ናዳ አክሲዮን ማህበር
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
- ቀበና ናዳ ገበያ ማእከል አክሲዮን ማህበር በሰሚት 72 የሚገኘውን 2B G+7 ቅይጥ ህንጻ የማጠቃለያ (ፊኒሺንግ) ሥራ ለማሰራት የህንጻ ወይም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ለማጫረት ይፈልጋል (labor Contract)::
- ጨረታው በመንግስት ግዥ መመሪያ ላይ በተገለፀው አሰራር አማካኝነት ይካሄዳል፡፡ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው:-
- 2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
- የንግድ ፈቃድ ምዘገባ፤
- የግብር መለያ ቁጥር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
- የወቅቱ ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት፤
- ለ2017 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሥራ አፈጻጸም ባለሥልጣን ወይም ከአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም
- የፒፒኤ ኦንላይን ምዘገባ ምስክር ወረቀት
- የግዢው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች ካለው አድራሻ የኢትዮጵያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) የማይመለስ ክፍያ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የማጠቀለያ (ፊኒሺንግ) ሥራ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል (በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም)፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ያስገቡና ታሽጎ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ አስራ አምስተኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከቀበና ናዳ አማ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሠሪው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ሞባይል፡- 09-11-20-20-16
ቀበና ናዳ አክሲዮን ማህበር
