በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የመሀል አምባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለመሀል አምባ ከተማ ለሚያሰራው የኮብልስቶን መንገድ (cobel stone road ) ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ
ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/16/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የመሀል አምባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለመሀል አምባ ከተማ ለሚያሰራው የኮብልስቶን መንገድ (cobel stone road ) ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም ለመንገድ ስራ GC/RC ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች፡፡
- በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ዝጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 50000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ / ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም::
- በወረዳው ውስጥ ሁለትና ከዚያ በላይ ፕሮጀክት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች መወዳደር አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡- 0113360162/146 ደደውሉ
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
