በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ቋሚ አላቂ እቃዎች ድርጅቶች/ ግለሰቦች አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር 0010/2017 ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ቋሚ አላቂ እቃዎች ድርጅቶች/ ግለሰቦች አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር 0010/2017 ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የሚያሳይ ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ወደ ዲላ በሚወስደው ዋና አስፓልት ከጨርቃ ጨርቅ ፊት ለፊት ባለው ላቄች ህንፃ ቢሮው ቁጥር 101 ሃብት አስተዳደር ስራ ሂደት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በሲፒኦ ያስያዙበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በግዢ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (supplier list) ላይ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል/ካለ/፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒክና የፋይናንሽል ሰነድ ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸጉ ፖስታ ለብቻ ለብቻ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 101 አንደኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር ስራ ሂድት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ከላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወደ ዲላ በሚወስደው ዋና አስፓልት ከጨርቃ ጨርቅ ቆት ለቆት ባለው ላቄች ህንፃ ምድር ላይ በሚገኘው ሻይ ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማብራሪያ ቢያስፈልግዎት የስልክ ቁጥር፡-046-2-12-65-02/ 046-2-12-56-90 ይጠቀሙ፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
