Tender Detail

Tender Details


ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየሰራ ለሚገኘው የተለያዩ ፕሮጀክቶች 1ኛ እንጅባራ ትራፊክ ኮምፕሌክስ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል 60/70 bitumen፤ prime coat (MC-30) እና Tack coat (RC-70)፤ 2ኛ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት የተለያዩ ceramic Tile: Pvc Tile: Adhesive አቅርቦት፤ 3ኛ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት Glazed Clinker Wall Tile አቅርቦትና ገጠማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-16/2017 እና 17/2017

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየሰራ ለሚገኘው የተለያዩ ፕሮጀክቶች፡-

 

1ኛ እንጅባራ ትራፊክ ኮምፕሌክስ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል 60/70 bitumen፤ prime coat (MC-30) እና Tack coat (RC-70)፤

2ኛ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት የተለያዩ ceramic Tile: Pvc Tile: Adhesive አቅርቦት፤

3ኛ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት Glazed Clinker Wall Tile አቅርቦትና ገጠማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ የንግድ ፈቃድ ለማደስ ግብር ስለመክፈላቸው የሚሰጥ ማስረጃ ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመካፈል የሚያስችል ሰርተፊኬት ማቅርብ የሚችሉ እና ለአቅርቦት እና ገጠማ ስራውን ከዚህ በፊት ለመስራታቸው የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  2. የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም unconditional bank guarantee በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. የጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ባህር ዳርዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 የግን/ግብ/ግዥ እና አቅርቦት ኬዝ ቲም ቢሮ ክፍል ነው::
  5. ውድድሩ በሎት /በጥቅል/ ዋጋ የሚታይ ሲሆን አስፈላጊ ከሆነ እና ለድርጅቱ (አዋጭ) ሆኖ ከተገኘ በእያንዳንዱ ወይም በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ሊለይ ይችላል፡፡
  6. ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለባቸው::
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

 

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡-

ባህርዳር :- 058-2-18-05-38/09-24-51-66-67/09-18-02-14-11/09- 13-27-60-57

አዲስ አበባ :- 011-1-26-56-52/-1-26-51-45/09-18-70-50-36

 

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን

 

Save Tender