Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-03 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአየር ንብረት ማስተካከል የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALMP4R) በፕሮግራሙ በጀት ድጋፍ ለሚደረግላቸው የዞን ግብርና መምሪያዎች ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የመረጃ ማደራጀትና ሪፖረት ስዎች ለማሳለጥ አገልግሎት የሚውሉ የላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢት/ግቢ/ግጨ/05/2017

 

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአየር ንብረት ማስተካከል የመሬት አያያዝ ፕሮግራም (CALMP4R) በፕሮግራሙ በጀት ድጋፍ ለሚደረግላቸው የዞን ግብርና መምሪያዎች ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የመረጃ ማደራጀትና ሪፖረት ስዎች ለማሳለጥ አገልግሎት የሚውሉ የላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ትሳተፉ ዘንድ ቢሮው ይጋብዛል።

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድና ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  3. የግዥ መጠኑ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን የተገናዘቡ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችና ፕሪንተር ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ)፦

ተ.ቁ

 የእቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

 ላፕቶፕ ኮምፒውተር

ቁጥር

130

 290,000.00

ሎት 2

 ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር

ቁጥር

30

 60,000.00

 

በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ (የጨረታ ማስከበሪያ ለቢሮው ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ በማያያዝ) ማቅረብ አለባቸው፡፡

  1. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስ መቶ ብር/ በመክፈል ከ10/07/2017 ዓም ጀምሮ እስከ 25/07/2017 ዓ.ም 04፡00 ሰዓት ድረስ በአብክመ ግብርና ቢሮ ባህር ዳር ዘወትር በሥራ ሠዓት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሀሳባቸውን በሁለት ፖስታዎች ማለትም በቴክኒካል ፖስታና በፋይናንሻል ፓስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡

የቴክኒካል ፖስታ መያዝ (ማካተት) ያለበት፡-

የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (specification) ፣ በዘርፉ እና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት የማቅረቢያ ጊዜ፣ የማቅረቢያ ቦታ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን እና የጨረታ ማስከበሪያ

    1. ፋይናንሻል ፖስታ መያዝ (ማካተት) ያለበት፡-

በዋጋ መሙያ ፎርም የተሞላ የእቃዎቹ ዋጋ ማቅረቢያ ብቻ ነው፡፡

  1. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ቅጅ (ኮፒ) በማዘጋጀት በፖስታው ላይ ዋና (ኦሪጅናል) ወይም ቅጅ (ኮፒ) መሆናቸውን የሚገልፅ ፅሑፍ በፖስታው ላይ በማስፈርና በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ11/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 26/07/2017 ዓ.ም 04፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረበ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 በ25/07/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡
  3. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግብርና ቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር+251-58-220-8771 በመላክ ፣ በስልክ ቁጥር +251-58-320-7115 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ ባህር ዳር

 

Save Tender