የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የውጪ ካፌ እና የላንድስኬፕ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የውጪ ካፌ እና የላንድስኬፕ ስራ ለማሰራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት
- ደረጃቸው GC/BC 6 እና ከዚህ በላይ የስራ ተቋራጮች 2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር መለያ ቁጥር (TIN Number) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም በሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች ፤ የስራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።
- በሲዳማ ክልል ውስጥ (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብቶ ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ የስራ ተቋራጮች ይህንን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
- በሲዳማ ክልል ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሰሪ እና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብቶ በስራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውንም ዓይነት የስራ አፈጻጸም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ስራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) ማወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (BID security) ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (Bank Guarantee) ወይም የክፍያ ማዘዣ ( CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የስራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 ብር (አምስት መቶ) ብር የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስሊፕ ይዞ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 208 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የስራ ተቋራጮች ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (BID BOND Security) ፋይናንሻል 1 ዋና (ኦሪጅናል) እና 2 ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና ኦሪጅናል እና 2 ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በታሸገ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በመክተት በሁሉም ዶክመንት ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት የሲዳማ ከልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቶች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡
- አሰሪው መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462125584 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
