በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንዕጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል::
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 23/2017
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንዕጽና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሐራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል:: በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጡ ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው::
- ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት C.P.O ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 0464441415/0464441564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
