የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለመንግሥት አገልግሎት ሥራ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ ውሃ ማዕድንና እና ኢነርጂ ቢሮ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለመንግሥት አገልግሎት ሥራ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶች አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
|
ተ/ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የሲፒኦ መጠን በብር |
ምርመራ |
|
1 |
ለኔትዎርክ መሰረተ-ልማት ግብዓት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች |
20,000 |
|
|
2 |
ለአውቶሜሽን አጋዥ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
||
|
3 |
ለኔትዎርክ መሰረተ-ልማት ዝርጋታ የሙያ ክፍያ |
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር _ ስለመክፈላቸው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች የመወዳደርያ ሃሳብ በመሙላት ዋጋቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የቫት (VAT) ሰርተፍኬትና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርን ክብ ማህተም እና ፊርማ ማኖር አለባቸው፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሲዳማ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 104 በአካል በመቅረብ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይቻላል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው (በአስራ አምስተኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ቢሮ ቁጥር 102 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ በመሙላትና አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ሁለት ቴክኒካል ኮፒ በማሸግ ደግሞ አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ፋይናንሻል ኮፒ በተለያየ ፖስታ ላይ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በእራሳቸው ፈቃድ በጊዜው አለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይቻልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፤ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሑድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣይ በሥራ ቀን ይሆናል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
