Tender Detail

Tender Details

  • Company Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋዜቦ አደባባይ ስተረሊንግ ህንጻ 3ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-552-7748
  • Websitehttps://tikurabaytl.com/
  • Deadline16 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Spare Parts

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በርከት ያሉ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎች የመኪና መለዋወጫ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Tikur Abay Transport PLC (ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማ/)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በርከት ያሉ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎች የመኪና መለዋወጫ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት በዚህ ጨረታ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች መለዋወጫዎቹ በሚገኙበት ኮምቦልቻ እና አዳማ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት በመሄድ የገዛውን የጨረታ ሠነድ ክፍያ በማሳየት መለዋወጫዎቹን ማየት ይችላል።
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ የመለዋወጫዎቹን ጨረታ መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማስገባት ውድድሩን መሳተፍ ይችላሉ።
  3. ሌላው በሚያቀርበው የጨረታ ዋጋ ላይ በመንተራስ በፐርሰንት አሳንሶ ወይም አስበልጦ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን ለተከታታይ 15 አስራ አምስት/ ቀናት ዘወትር በስራ ሠዓት ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አዲስ አበባ ማስ/ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ በኩባንያው ዋና መ/ቤት ፋይናንስ ክፍል እንዲሁም አዳማ እና ባህር ዳር በኩባንያው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን በመሙላት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው የጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት አዲስ አበባ እና ኮምቦልቻ በሚገኘው የኩባንያው መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ መዝጊያው ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በስራ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እና በኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ መክፈል ይጠበቅባቸዋል በአስር ቀን ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ካልቻሉ አሸናፊነታቸው ተሰርዞ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስላቸውም፡፡ አሸናፊዎች ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ እስከ 15 ቀን ድረስ እቃዎቹን በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን በተባለው ጊዜ ውስጥ እቃዎቹን ማንሳት ካልቻሉ በቆየበት ጊዜ ልክ የመጋዘን ኪራይ የሚከፈል መሆኑን እናሳውቃለን።
  8. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
  9. ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 011-552-77-48 ወይም 011-557-38-24


ጥቁር ዓባይ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ
ኃላ.የተ.የግል ማህበር

Save Tender