Tender Detail

Tender Details

  • Company በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግዥ ስራ አስፈፃሚ
  • Address አማራ ኢትዮጵያ, Phone: 0118900329
  • Website
  • Deadline16 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Laboratory Equipment And Chemicals

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ Medicine /መድኃኒቶች/፣ Medical and Pathology supplies & Laboratory reagents and chemicals /ላቦራቶሪ ሪኢጀንትና ኬሚካልስ/ መግዛት ይፈልጋል

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግዥ ስራ አስፈፃሚ


የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር DBU/AWHSC/04/2017

 

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለሐኪም ግዛው ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ቀጥለው የተዘረዘሩትን ግብዓቶች ማለትም:-

  • ምድብ 1፡ Medicine /መድኃኒቶች
  • ምድብ 2፡ Medical and Pathology supplies
  • ምድብ 3፡ Laboratory reagents and chemicals /ላቦራቶሪ ሪኢጀንትና ኬሚካልስ/

በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በማዕቀፍ ውል መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፦

  1. ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃና ከኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለምድብ- 1 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለምድብ-2 ብር 70,000 (ሰባ ሺህ ብር)፣ ለምድብ-3 ብር 90,000 (ዘጠና ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ጋራንት፤ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1000655215054 ገቢ በማድረግና በካምፓሱ ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ቢሮ ቁጥር F- 03 ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ማህተም  በማስደረግ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G -01 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ (Original and copy) ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርሲቲው የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G- oı ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ጠዋት 4፡30 ላይ የዋጋ ሰነድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ከስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እና ከውስጥ ኦዲት ስራ አስፈፃሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት በካምፓሱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-01 በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ዕለቱ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል ትክክለኛውን የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ እንገልፃለን።
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሰረት በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሐኪም ግዛው ማስተማሪያ ሆስፒታል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ድርጅቶች በስልክና በደብዳቤ እንዲሁም በካምፓሱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የምናሳውቅይሆናል። ተጫራቾች በሚወዳደሩት ሰነድ ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት የሚሰሩ ስልኮችን ማስቀመጥ አለባቸው።
  9. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011 890 0329 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

 

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ

ካምፓስ ግዥ ስራ አስፈፃሚ

 

 

 

Save Tender