Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-11-48-00
  • Website
  • Deadline10 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Works

በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፊያ ግንባታ እና የጥገና ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮማሰራት ይፈልጋል

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብግጨ 003/17

 

በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፊያ ግንባታ እና የጥገና ስራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮማሰራት ይፈልጋል

በመሆኑም፦

  • እያንዳንዱ ተቋራጭ ድርጅት የሚከተሉትን ነጥቦች በመገንዘብየጨረታ ሰነዱን መስሪያ ቤታችን ድረስ በግንባር በመቅረብመግዛትና መወዳደር ይችላል።
  1. ተጫራቾች የስራ ፈቃድ ኖራቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እናክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣በመንግስት የግዥ ቋት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀትና የተጨማሪእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እና የብቃትማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የስራ ውል ያላቋረጡ መሆንይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በአንድ ወገን ውል አቋርጦ የነበረተጫራች ከተገኘ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል።
  3. የጨረታ ሰነዱን በሁለት ፖስታዎች ዋና /original እና ቅጂ /copy/ ኤንቬሎፕ ታሽጎ በጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስረከቢያ ሰዓትከመድረሱ በፊት በቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍልመግባት ይኖርበታል።
  4. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 /አስራአምስት ሺህ ብር/ CPO እና በጥሬ ገንዘብ ከዋናው (original) የጨረታሠነድ ውስጥ አድርጎ ማቅረብ ይኖርበታል።
  5. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ጨረታ አየር ላይከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 / አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት መስሪያቤታችን በግንባር በመገኘት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  7. የጨረታ ሠነድ መቀበያ ሰዓት ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይምበከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05

ጊዮርጊስ አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት

ስልክ ፡-0111 114 800

በአራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት 

የቤተልሔም ሁለተኛ ደረጃት/ቤት

Save Tender