የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመትሊያሰራ ላቀደው የሸገድና ወረዳ ዲላ አፋራራ ፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከልአጥርና የጥበቃ ማማ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽጨረታአወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመትሊያሰራ ላቀደው የሸገድና ወረዳ ዲላ አፋራራ ፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከልአጥርና የጥበቃ ማማ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽጨረታአወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ፡-
- ደረጃቸው GC-6/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾችየ2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትኮንስትራክሽን ባለሰልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትማቅረብ የሚችሉና እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆንአለባቸው።
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎችሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅአለባቸው።
- በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውልገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይሆንየጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውልገብተው በስራ ወቅት ከአሰሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤትማንኛውም አይነት የስራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ስራተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
- የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፣ ይህተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩከውድድር ውጭ ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 120,000.00 (አንድ መቶሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይምበሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊፈቃዳቸውንና ተዕታ (VAT) የተመዘገበበትን ሰርተፊኬትና ታክስክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበትቀን አንስቶ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽንፋይናንስ ከፍል በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይትበራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታማስከበሪያ (bid bond/security) f ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እናሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለትኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽገውበአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምናአድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6፡00 ሰዓትበሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስ ክፍልለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይበተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመግኘት የጨረታውን መከፈትአያግደውም።
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይምሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሰረትለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብይኖርበታል።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነበሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆና።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን
