Tender Detail

Tender Details

  • Company በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 01 ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0118160211
  • Website
  • Deadline08 Mar 2025, 5:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች በ 2017 ዓ.ም በጀት አመት ከታች የገለጹትን እቃዎች በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 01 ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጨረታ ቁጥር 002 / 2017 ዓ.ም

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች በ 2017 ዓ.ም በጀት አመት ከታች የገለጹትን እቃዎች በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  • ሎት 1) የደንብ ልብስ
  • ሎት 2) ቋሚ ዕቃ   ከላይ የተገለጹትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው ሰነድ ገዝተው መወዳደር ይችላሉ።

  • ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል የዘመኑ ግብር የገበረ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች እያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታው የእቃውን ዝርዝር ሰነዱን ላይ ያለውን ብቻ መሰረት ማድረግ ይኖርባችኋል።
  • የጨረታ ማስከበርያ በእያንዳንዱ ሎት ሎት 1) 20,000 ብር ( ሃያ ሺ ብር) ሎት 2) 20,000 ብር (ሃያ ሺ ብር) CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ የሚጫረቱባቸውን የእቃዎች በሙሉ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው።
  • የጨረታ ማስከበርያ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለአንድ ጨረታ ሰነድ በመክፈል በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ መውሰድ ይችላል።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው። መስርያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በጨረታው ሰነድ ውስጥ መ/ቤቱ ከጠቀሳቸው የእቃዎች ዝርዝር ውጪ ያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ።
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበርያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው
  • ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበት አሸናፊው ከተለየበት አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል።
  • ተጫራቾች የጨረታው ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  • ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት በየሎቱ CPO ማስያዝ አለባችሁ ጥቅል CPO ካስገቡ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ።
  • በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ጨረታ ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ይሆናል በማያመርቱ ምርት ላይ ሰነድ የሚገዙ ይሆናል።
  • በጨረታ ሂደት ላይ ለማሳሳትና የማጭበርበር ስራ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ህጉ በሚያዘው በኢትዮጵያ ህግ የሚዳኝ ይሆናል።
  • ለቋሚ እቃዎች ናሙና ለማይቀርብላቸው የእቃዎቹ እስፔፊኬሽን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ፖስታው ኮፒ ና ኦርጅናል በማሸግ ማስገባት አለባቸው። CPO ውን ኦርጅናሉን ሰነድ ላይ ማያያዝ አለበት ኮፒ ላይ ከተደረገ ከጨረታው ላይ ተሳታፊ አይሆኑም።
  • ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን የጨመረ መሆን አለበት።
  • ማንኛውም ተጫራች በጨረታው አፈጻጸም ሂደት ላይ ቅሬታ ቢኖረው በ5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ። በ6ኛው ቀን ቅሬታ ማቅረብ አይችሉም።
  • ለጨረታ የቀረቡትን የእቃ ናሙናዎች ውጤት በተገለጸ በ10 ቀናት ውስጥ እቃዎችን መውሰድ አለባችሁ ይህ ባይሆን እቃዎቹ ለመስርያቤቱ ገቢ ይሆናል።
  • ጨረታውም አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል 10ኛ ቀን ላይ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ይሆናል በ11ኛው ቀን ሰነድ ማስገባት አይቻልም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ቢኖሩም ባይኖሩም የሚከፈት ይሆናል።
  • ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ቦሌ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ የግዥ ቡድን መሪ መጠየቅ ይቻላል።
  • አድራሻ፡- ቦሌ ሚካኤል ከጉምሩክ ወረድ ብሎ ኮንደምንም ጀርባ ወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 816 0211
በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 01 ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት

Save Tender