በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተያዘለት በጀት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በአ.ብ.ክ.መ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ(Kombolcha City Administration City and Department of Infrastructure)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተያዘለት በጀት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- አገልግሎት አቅራቢነት ቲን ነምበር ያላቸው
- የግዥው መጠን ከ200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና ኦሪጅናል ከሰነዱ ጋር በፖስታ አሽጋችሁ ይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል፣
- የጨረታ ሰነዱን ከ20/06/2017 እስከ 4/07/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከኮ/ቻ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 25,000 /ሃያ አምስት ሽህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ከሆነ ኦሪጅናሉን፣ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባችኋል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 16 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 5/07/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት ሳጥኑ የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተጫራቾች ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅብዎታል።
- በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በስልክ ቁጥር 0333519107 ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
- ጨረታው ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
- አሸናፊ የምንለየው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው።
- መምሪያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአ.ብ.ክ.መ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከተማና
መሰረተ ልማት መምሪያ
