የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (Sidama National Regional Government Livestock Development Office)
የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 08/07
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ፈሳሽ ናይትሮጂን መያዣ ኮንቴነሮች (ለ2ኛ ጊዜ)፣ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ (ኤይርታግ እና አፒሊከተር ለ2ኛ ጊዜ)፣ የፈሳሽ ናይትሮጂን ማሽን መለዋወጫ ዕቃ (ለ3ኛ ጊዜ) ባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል (ለ2ኛ ጊዜ)፣ የውሃ ፓምፕ (ለ2ኛ ጊዜ)፣ የ48 ቀን ጫጩት (ለ2ኛ ጊዜ)፣ ለእንስሳት ጤና ክሊንክ የሚያስፈልግ ፈርኒቸር (ለ2ኛ ጊዜ) እና ዶሮ መኖ መመገቢያና ውሃ መጠጫ ቁሳቁስ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
-
-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣ጨረታ መሳተፍ የሚችልና የምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል/ የምትችል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት ቀን) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ/እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸው አማካይነት መግዛት ይቻላል።
- በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /Bank GAURANT/ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክንካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
- አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት። ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ኬዝ ቲም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
- የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
-
ሀ) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 10 83 60/09 16 07 00 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ/ብ/ክ/መ/እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ
