Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
  • Address ሚዛን አማን : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0471355629
  • Website
  • Deadline13 Mar 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የሙዚቃ መሳሪያዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ


ለሁለተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የሙዚቃ መሳሪያዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ወይም በተዛማጅ ስራዎች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የሙዚቃ መሳሪያዎች ግዥ 50,000 (ሃምሳ ሽህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
  8. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 135 5629

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender