ለጤና ባለሙያዎች የሚዉሉ ጨርቃ ጨርቆች እና አልባሳት /ደንብ ልብስ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Yirgalem Medical college (የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 4/2017 ዓ.ም
የይ /ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ በህክምና ኮሌጅ ውስጥ ተኝተው እና ተመላልሰው ለሚታከሙ መድኃኒት ለተላመደ የሳንባ በሽታ /MDRTB/ ታካሚዎች አገልግሎት የሚውል
- የምግብ ግብአቶች፣
- መድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣
- የላቦራቶሪ ሪኤጀንት፣
- ለጤና ባለሙያዎች የሚዉሉ ጨርቃ ጨርቆች እና አልባሳት /ደንብ ልብስ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸዉ፣ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ስፒኦ/ ማስያዝ የሚችሉ፤
- በጨረታ ለመወዳደር ከገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጣቸውን ማስረጃ /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃዳቸዉን ተ.እ.ታ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት እና ሌሎች ይጠቅሙናል የምትሉትን ማስረጃዎች በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ በአንድ ፖስታ 1ኛ. አንድ ኦርጅናል የቴከኒክ እና አንድ ኦርጅናል ፋይናሻል ሰነድ፣ 2ኛ ሁለት የቴክኒክ እና ሁለት ፋይናሻል ኮፒ ሰነድ በተለያዬ ፖስታ በሰም ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ እና ቁልቁል ተደምሮ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ በ15ኛው ቀን እስከ 6፡፡0 ሰዓት ድረስ ይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ15ኛዉ ቀን ከቀኑ 6፡30 /ስድስት ሰዓት ተኩል/ ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል።
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያዝ አለበት።
- ተወዳዳሪዎች በዝርዝር የተቀመጡትን ግብአቶች ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- አሰሪው መስሪያ ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 66 90 16 81/ 09 09 49 545 መደበኛ 046 225 0769 ይደውሉ።
የይ/ዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ
