በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለሰሜን ጎንደር ዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል ሎት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና እስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
North Gondar Zone Finance Department(የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለሰሜን ጎንደር ዞን መምሪያዎች አገልግሎት የሚውል ሎት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና እስቴሽነሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፍቃድ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 /አንድ ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ለግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከ1% ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሰ/ጎ/ዞ/ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ 20/06/2017 እስከ 04/07/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በቀን 05/07/2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እና እስቴሸነሪ የሚያቀርበው ሰ/ጎ/ዞን ባሉት ንብረት ክፍል በአካል ይሆናል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
- የጨረታ ውድድር አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በድምር ዝቅተኛ ዋጋ ነው።
- የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- የጨረታው የመክፈቻ ቀን እሁድ፣ ቅዳሜ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058-4-17-01-26 መጠየቅ ይችላሉ።
የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ
