የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎቹ የሚገልፅ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት /በመቅረብ/ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል።
-
- ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ለማቅረብ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 15,000 በባንክ በተመሰከረ C.P.O /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30-1፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8:00 ተዘግቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። የመክፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
የተወዳዳሪ ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል።
የተወዳዳሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀን አይለውጠውም።
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 092 005 7024/091 321 3696 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
