Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline13 Mar 2025, 11:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Construction

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአሰላ የህንጻ ማሳመር ስራ፣ በአቦምሳና በደሎመና የሻወርና የሽንት ቤት ስራ እንዲሁም በአለምጤና፣ በመቂ እና በቆቃ የጥበቃ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤትና የአጥርስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአሰላ የህንጻ ማሳመር ስራ፣ በአቦምሳና በደሎመና የሻወርና የሽንት ቤት ስራ እንዲሁም በአለምጤና፣ በመቂ እና በቆቃ የጥበቃ ቤት፣ ደረቅ ሽንት ቤትና የአጥርስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የታደሠ ፈቃድ ያላቸውና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የጨረታው መስፈርቶች፣

  1. ጨረታው ከየካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒአ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-11-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም

ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

 

Save Tender