Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118212214
  • Website
  • Deadline11 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Others

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ010/2017 የኢንተግሬትድ ጂፒኤስ ትራኪንግ እና ነዳጅ መቆጣጠሪያ ስርዓት /Supply, Installation, Configuration and Maintenance of Integrated Real Time Tracking (GPS Based) and Fuel Management System (Sensor Based) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ010/2017 የኢንተግሬትድ ጂፒኤስ ትራኪንግ እና ነዳጅ መቆጣጠሪያ ስርዓት /Supply, Installation, Configuration and Maintenance of Integrated Real Time Tracking (GPS Based) and Fuel Management System (Sensor Based) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)
  2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣
  3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ኮፒ (VAT Certificate)
  5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate):
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ በ15ኛው ቀን ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን የበአላት ቀን የሚውል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ ፡-

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር: 0118 21 22 14

 

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender