Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Blood and Tissue Bank Service (የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት)
  • Address Ethiopia, Phone: 0911 76 11 59
  • Website
  • Deadline10 Mar 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎችን፣ ብረታ ብረቶችንና የመኪና ጎማዎችን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል::

Ethiopian Blood and Tissue Bank Service (የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት)


 

ያገለገሉ ዕቃዎች፣ ብረታ ብረቶችና የመኪና ጎማዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ልዩ ልዩ ያገለገሉ ዕቃዎች፣ ብረታ ብረቶችና የመኪና ጎማዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-001/2017

 

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎችን፣ ብረታ ብረቶችንና የመኪና ጎማዎችን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል::

በመሆኑም ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ሠንጋ ተራ ጎማ ቁጠባ አካባቢ በጤና ሚኒስቴር ግቢ በምዕራብ በኩል ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን 3ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በነጻ በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይቻላል::

  1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎችን፣ ብረታ ብረቶችንና የመኪና ጎማዎችን ዋናው መ/ቤታችን ግቢና በአዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ በመገኘት በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው የመ/ቤቱ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
  2. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 8፡15 ሰዓት ላይ በመ/ቤቱ ዋና መሥሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል::
  3. 15ኛው ቀን የበዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የብር 10,000.00 (አስር ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ስልክ ቁጥር፡- 0911 76 11 59 ወይም 0913 46 43 39

ተጨማሪ የጨረታ ማስታወቂያዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገጻችንን እና የፌስቡክ ገጻችንን ይጎብኙ!

ቴሌግራም፦ @EBIBS

ፌስቡክ ፡- Ethiopia Blood & Tissue Bank Service

 

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት

 

Save Tender