በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳት የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ መገናኛ እና ኮምውተር ዕቃዎች፣ መለዋጫዎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ ባለሁለት እና ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 09-2017
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ አልባሳት የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ መገናኛ እና ኮምውተር ዕቃዎች፣ መለዋጫዎች የቤት ውስጥ መገልገያ ዕቃዎች፣ ባለሁለት እና ባለ ሶስት እግር ተሸከርካሪዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በተሽከርካሪዎች ጨረታ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከተሽከርካሪ አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተራ ቁጥር 1. የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚገልጽ “ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 1. የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም/ አያስፈልግም፡፡
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ለሐራጅ ጨረታ የቀረቡትን ደግሞ አስከ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡
- ለግልፅ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2017ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የግልጽ ጨረታው የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት ኣካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡15 ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን፤ በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
- የሐራጅ ጨረታው የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፤
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ በ5 /በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 10 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋስትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
- በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጪ ማድረግ አይችልም፡፡
- በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ መብቱ አይሸፍንም፣፣
- ለግልፅ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ለግል ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልከ ቁጥር 058-320-74-18/058-320-75-69 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
