በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት G+4 አስተዳደር ህንጻ የውቅር /structural parts of the Building/ ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት G+4 አስተዳደር ህንጻ የውቅር /structural parts of the Building/ ግንባታ ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
- እስከ GC ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በBC ለሚወዳደር ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያለው መሆንና የበጀት ዓመቱ የታደሰ የኮንስትራክሽን የብቃት ማረጋገጫ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው፣ (የቫት) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤ በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኦን ላይን የተመዘገቡና ከሰነዱ ጋር ማያያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) 375,000.00 (ሶስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ከሚያቀርቡት ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ማለትም አንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ሁለት (ቅጂ) ኮፒ፣ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ሶስት ቅጂ /ኮፒ/ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል።
- ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ላይ በምስራቅ መስቃን ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 ላይ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ፣ የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዳቸው ሰነድ የማይመለስ ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ በመክፈል ምስራቅ መስቃን ወረዳ 4/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/የስራ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በቀድሞው 2010 በወጣው መመሪያ በደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ /Arithmetic Error/ 2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 04-63-21-01-58
ማሳሰቢያ ፡- የህንጻው ግንባታ የሚከናወንበት ቦታ ተጫራቾች ከጽ/ቤቱ ከአስተዳደሩ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ቦታውን መጎብኘትና መጎብኘታቸውን የሚያስረዳ መረጃ ከሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ልብ ይበሉ፡- ተወዳዳሪዎች የምታስገቡት ሰነድ የተጭበረበረ /ፎርጅ/ fraudulent/ ዶክመንት ከሆነ ከጨረታ ውጭ ተደረጎ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን የምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
