Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጦርሀይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ 700ሜ ገባ ብሎ ኪዳኔ ጉበሬ ህንፃ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 -3713324
  • Website
  • Deadline05 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ለባለ በጀት መስሪያ ቤቶች መጠቀሚያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2017

 

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ለባለ በጀት መስሪያ ቤቶች መጠቀሚያ ዕቃዎች :-

  • ሎት 1፡- የደንብ ልብስ /ካኪፖሊስተር፣ አጭር የወንድ ቆዳ ጫማ፣ አጭር የሴት ቆዳ ጫማ እና አንፀባራቂ/
  • ሎት 2:- የፅህፈት መሳሪያ የፎቶኮፒ የፕሪንተር ወረቀት ፣ ሀርድ ከቨር/
  • ሎት 3:- የጽዳት ዕቃ /ላርጎ
  • ሎት 4:- ልዩ ልዩ /ማከፋፈያ፣ ማውዝ/
  • ሎት 5:- የመኪና ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የጨረታው መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
  1. ለሎት 1፡-5000 ብር፣ ለሎት 2፡-15,000 ብር፣ ለሎት 3፡- 4000 ፣ ለሎት 4: 3000፣ ለሎት 5: 4000 በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 በመክፈል ከል/ክ/ከ/ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው እቃዎች በእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ ላይ ቫት ጨምረው መሙላት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት በሰጠው ናሙና መሰረት ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ሎቶች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሽናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7/በሰባት/ ቀን ውስጥ የውል ስምምነት ማስከበሪያ ባሸነፈበት ጠቅላላ ብር ላይ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ንብረት ውል በገባ በ15 ቀን ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. በአንድ ዕቃ ላይ ሁለት የተለያየ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
  12. ተጫራቾች በምዝገባ ፈቃድ ጀርባ የሚገኘው የስራ መስከ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስራ አንደኛው (11ኛው) ቀን በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/2/ፋ/ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
  14. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  15. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ፡- ጦርሀይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ 700ሜ ገባ ብሎ ኪዳኔ ጉበሬ ህንፃ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ስልክ ቁጥር 011 -3-71-33-24 /011- 3-71-33-21

 

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender