በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ አባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም-5 በካፒታል በጀት የተለያዩ ቁሣቁሶችን ግልጽ በሆነ ጨረታ አወዳድሮ በጥቅል መግዛት ይፈልጋል።
በጋሞ ዞን የምዕራብ አባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ አባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም-5 በካፒታል በጀት የተለያዩ ቁሣቁሶችን ግልጽ በሆነ ጨረታ አወዳድሮ በጥቅል መግዛት ይፈልጋል።
የዕቃዎች ዓይነት
-
- አሸዋ ፤ ድንጋይና ጠጠር ግዥ ከነ ማጓጓዣ
- የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ
- የችግኝ ዘርና ችግኝ ሳዮን ግዥ
- የንብ ቀፎና ቁሳቁስ ግዥ
- የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
- የባህር ዛፍ እንጨት ግዥ
በዚሁ መሠረት
1/ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
2/ የግብር ከፋይነት መለያ/ቲን/ ቁጥር ያለው፤
3/ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው (በEGP) ኦንላይን የተመዘገበ ፤
4/ የችግኝ ዘርና ችግኝ ፤ ሳዮን ግዥ ውጪ የሁሉም ዕቃ ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
5/ የጨረታው ሣጥን ም/አ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ይገኛል፡
6/ የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች እና የቤትና የቢሮ ዕቃዎች እስከ ምዕራብ አባያ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ድረስ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ብሎኬት እስከ ተጠቀሰው ቀበሌ ማቅረብ የሚችል፡፡
7/ የመኪና ኪራይ እነዲሁም የጫኝና አውራጅ ዋጋ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል።
8/ አሸዋ ድንጋይ ጠጠር፤ ብሎኬት የንብ ቀፎ ችግኝና የባህር ዛፍ እንጨቶች ሰነዱ ላይ በተጠቀሱት ቀበሌ ለማራገፍ ፍቃደኛ የሆነ፤
9/ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች 30,000 ፤ ለአሸዋ ድንጋይና ጠጠር ግዥ ከነማጓጓዣ 20,000 የንብ ቀፎና ቁሳቁስ ግዥ 20,000፤ ለቤትና ቢሮ ዕቃዎች 15,000 ለባህር ዛፍ እንጨት 3,000፤ የችግኝ ዘርና ችግኝ ሳዮን ግዥ 15,000 በባንክ በተመሠከረለት CPO ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10/ ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በወረዳው ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ደረሠኝ በመያዝ ወደ ም/አ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ ዋና የሥራ ሂደት በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
11/ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ለይቶ በፖስታ በማድረግ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ አድርጎ በማሸግ በላዩ ላይ ህጋዊ የድርጅቱን ማህተም ስምና ፊርማ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።
12/ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
13/ አሸናፊው ድርጅት ያቀረበው ዕቃ ጥራቱ በባለሙያ ታይቶ ገቢ ይሆናል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር - 0970853470 / 09160100212 / 0926142310 / 0922142120
በጋሞ ዞን የምዕራብ አባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
