ድርጅታችን በመከኒሳ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኙት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክስ ቅብ (Epoxy Painting) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
National Alcohol and Liquor Factory (ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 040/2017 ዓ.ም
ድርጅታችን በመከኒሳ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኙት የሞላሰስ ማከማቻ ታንከር ኢፖክስ ቅብ (Epoxy Painting) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
- የታደሰ ፍቃድና የዘመኑ ግብር ለመክፈላችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፤
- የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መከኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ገንዘብ ቤት ቢሮ ቁጥር 004 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
- ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት መከኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ፖ.ሣ.ቁ. 3516 ስልክ ቁጥር 011 369 0563 ፋክስ 011 5 513299
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
