Tender Detail

Tender Details

  • Company የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና/አስ/ ቡድን ደ/ወርቅ
  • Address ደብረወርቅ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0586630023
  • Website
  • Deadline15 Mar 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Road And Bridge Construction

በአብክመ በምስ/ጎጃ/ አስ/ዞን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና/ን/አስ ቡድን ለእናርጅ እናውጋ ወረዳ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ ካፒታል በጀት ሎት 1፡- መንገድ ጥገና ከዋናው መስመር የዲጥ ቀበሌ ማእከል ድረስ ሎት 2 ፡- መንገድ ጥገና ከመጠያ ታዳጊ ከተማ ጓሮ ገደል ቀበሌ ማእከል ድረስ ሎት 3፡- ለገደብ ጤና ጣቢያ ካርድ ክፍል ግንባታ እና ሎት 4፤ ለደብረወርቅ ሆስፒታል ካርድ ክፍል ግንባታ እንዲገነባላቸው እና መንገድ እንዲጠገንላቸው በጠየቁት መሰረት ግንባታውን እና ጥገናውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን እና ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና/አስ/ ቡድን ደ/ወርቅ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በምስ/ጎጃ/ አስ/ዞን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና/ን/አስ ቡድን ለእናርጅ እናውጋ ወረዳ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ ካፒታል በጀት ሎት 1፡- መንገድ ጥገና ከዋናው መስመር የዲጥ ቀበሌ ማእከል ድረስ ሎት 2 ፡- መንገድ ጥገና ከመጠያ ታዳጊ ከተማ ጓሮ ገደል ቀበሌ ማእከል ድረስ ሎት 3፡- ለገደብ ጤና ጣቢያ ካርድ ክፍል ግንባታ እና ሎት 4፤ ለደብረወርቅ ሆስፒታል ካርድ ክፍል ግንባታ እንዲገነባላቸው እና መንገድ እንዲጠገንላቸው በጠየቁት መሰረት ግንባታውን እና ጥገናውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን እና ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ TIN/ ያላቸው
  3. ተወዳዳሪዎች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው
  4. ተወዳዳሪዎች የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው ::
  5. የመንገድ ጥገና ተወዳዳሪዎች ከደረጃ RC/ GC 6 /ስድስት/ እና ከዚያ በላይ እንዲሁም የካርድ ክፍል ግንባታዎች ከደረጃ GC/ BC 7 /ሰባት/ እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
  7. የሚሰራው ስራ ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለማንኛውም ግለሰብ በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ሲሆን በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ በማፃፍ በነፃ ከግዥና ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት የሚቻል ሲሆን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ግን ተቀባይነት የለውም። የሚፃፈው የድጋፍ ደብዳቤ ኢንተርፕራይዝ የተደራጀበት ቀን እና ዓ.ም መጠቀስ አለበት።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልስ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት 1:- ብር 20000 (ሃያ ሺህ ብር) ሎት 2፡- ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሎት 3፡- እና ሎት 4- ለእያንዳዳቸው ብር 6000 (ስድስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ- 1 ግቢ በማድረግ መሂ - 1ን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ22ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ እለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ (ቅዳሜ እና እሁድ) ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው በተጠቀሰው ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት በመያዝ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዥ ውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል።
  12. አሸናፊው ተጫራች ግንባታውን ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 25% ከመሀንዲስ ግምት ዝቅ ብሎ ከሞላ፣ cost break down እና project work schedule እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ /conformation letter/ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት፡፡
    • የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ አሸናፊ ሆነው የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጭ ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፣
    • የውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ፣ CPO ፣ጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሞላውን ዋጋ 10 በመቶ የነበረው ተሻሽሎ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል፤
  13. ለግንባታው የሂሳብ ስሌትን በተመለከተ /አርቲሜቲክ ቼክ/ በግዥ መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  14. የስራ ዝርዝሩ መተርጎም ካለበት የማስተርጎሚያ ወጭ እንዲሁም ውል ለመያዝ የሚያስፈልጉ ሌሎች ወጪዎች ካሉ አሸናፊው ተጫራች መሸፈን የሚችል ይሆናል፤
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር-7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0586630023 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

 

የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና/አስ/ ቡድን

ደ/ወርቅ

 

 

Save Tender