በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ለሞ/ወ/ወ/ መስ/ቆላ/አካ/ል/ ጽ/ቤት የአነስተኛ መስኖ ምንጭ ማጎልበት የመስኖ አውታር ግንባታ ለሞ/ወ/ወ/መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ለሠላድንጋይ መናሃሪያ የእንግዳ ማረፊያ ሼድ ስራ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል::
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ለሞ/ወ/ወ/ መስ/ቆላ/አካ/ል/ ጽ/ቤት የአነስተኛ መስኖ ምንጭ ማጎልበት የመስኖ አውታር ግንባታ ለሞ/ወ/ወ/መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ለሠላድንጋይ መናሃሪያ የእንግዳ ማረፊያ ሼድ ስራ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ 1 ማስያዝ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለተከታታይ 16 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል:: ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል:: ለግንባታ ጨረታ ለ21 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸው ለእቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ለግ/ንብ/አስ/ቡድን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
- የጨረታ መዝጊያ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፣
አድራሻ ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር (ዋሻ) ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
