Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Maintenance And Repair

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- ኢኘድ 006/2017

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የፅዳት አገልግሎት

ሎት 2. የፕሪንተሮች እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ጥገና አገልግሎት

ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር ለሎት 1. ብር 36,000 (ሠላሳ ስድስት ሺህ) ለሎት 2.ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ቢድቦንድ ማስያዝ አለባቸው::
  4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ አቅርቦት መምሪያ ክፍል ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አሮጌው ፎቅ በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ምድር ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69 ኢሜይል procurement@press.et

አድራሻ :- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

 

 

የኢትዮጵያ ኘሬስ ድርጅት

 

Save Tender